የዓባይን ልጅ ውሃ ጠማው ...ሆነ ነገሩ
ኢትዮጵያ በጥንታዊ የጽሁፍ ሀብታቸው በተለይም በግዕዝ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛና በአጃሚ ከሚታወቁ ጥቂተ የዓለማችን ሀገሮች አንዷ ናት፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነ-ልሳን ትምህርት ክፍልም በዚሁ ሃብት ላይ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የፊሎሎጂ ትምህርት በማስተርና በፒኤችዲ ደረጃ መስጠት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ይሁንና የጽሁፍ ሃብቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኙ ተቋማት ማለትም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፓትርያርኩ ቤተመጻህፍት፣ አድባራትና ገዳማት፣ አዲስ አበባ የዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋምና ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት አኤጀንሲ ሲሆኑ እነዚህ ተቋማትም ባላቸው ደካማ የሆነ የአስተዳደር ፍልስፍናና ዝቅተኛ የምርምር ዕውቀት ሳቢያ ከዘራፊዎች፣ ከነፍሳት፣ ከውሃና ከእሳት የተረፉትን እንዲሁም በማይክሮ ፊልም ተቀርጸው በአውሮፓና በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በገፍ የሚገኙ የብራና ጽሁፎችን ቅጂ በተለይም ለኢትዮጽያውያን ለተመራማሪዎች በዘመናዊ መንገድ አዘጋጅቶ ከማቅረብ ይልቅ በፍጹም ከልክሎ እንዲሁ በየግምጃ ቤቶች አነባብሮ በማስቀመጥ ለዝርፊያና ለብልሽት ማጋለጥን መርጠዋል፡፡
በተቃራኒው በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች የኢትዮጵያን ጥንታዊ የጽሁፍ ሃብት ያከማቹ ምዕራባውያን መጻህፍቱን ለተመራማሪዎች ምቹ በማድረግ የተመራማሪዎችን ጭንቀት ከማቃለላቸው ባሻገር ትልቅ የገቢ ምንጭ ሆኖላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እኔን ጨምሮ የፊሎሎጂ ትምህርታቸውን በአአዩ በመከታተል ላይ የምንገኝ ተመራማሪዎች ከችግሩ ግዝፈት የተነሳ አንድን በኢትዮጽያ ውስጥ በተለይም በአዲስ አበባ የዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ውስጥ የሚገኝን ጥንታዊ ጽሁፍ ቅጂ ከማግኘት ይልቅ በእንግሊዝ፣ በጣልያን፣ በጀርመን፣ በፈረንሳይ ወይም በአሜሪካን ሀገር ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ቤተመዛግብቶች ማግኘት በእጅጉ ይቀለነናል፡፡ ለምሳሌ እኔም በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት አኤጀንሲ ክምቸች ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጥንታዊ የብራና ጽሁፎችን ቅጂ ለማግኘትና ለማጥናት የሀገሬ ተቋማት የከከሉኝን በአሜሪካን ሀገር በሴንት ጆንስ ዩኒቨርስቲ Alcuin Library ውስጥ የሚገኘው የHMML ሙዚየምና ላይብረሪ ፈቅዶልኝ መጻህፍቱን በማጥናት ላይ እገኛለሁ፡፡ የሚገርማችሁ አንድ የኢትዮጵያ ብራና ጽሁፍ ቅጂን ለማግኘት 68 የአሜሪካን ዶላር መክፈል ይጠበቅብኛል፡፡የዓባይን ልጅ ውሃ ጠማው ... አልሆነም ነገሩ ትላላችሁ?
ስለሆነም እባካችሁ የሚመለከተታችሁ አካላት በገዛ ሀብታችን የሰው እጅ እንድናይ አታድርጉን፡፡ ኢትዮጵያውያን የፊሎሎጂና የታሪክ ተመራማሪዎችንም ተስፋ አታስቆርጡን፡፡ እኛ ተመ
ራማሪዎቹ በተደጋጋሚ ጠየይቀነናቸው አልቀበልም ስላሉን ይሰሟችሁ እንደሆነ እባካችሁ ድምጻችንን አሰሙልን፡፡

No comments:
Post a Comment